እንግሊዝ ለዓለም አቀፍ ረኀብ ቴክኖሎጂን እንደ መፍትሔ አቀረበች

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

እንግሊዝ ለዓለም አቀፍ ረኀብ ቴክኖሎጂን እንደ መፍትሔ አቀረበች

በምግብ ዋስትና ዕጦት ላይ የተካሔደውን ዓለም አቀፍ ስብሰባ፣ ትላንት ሰኞ ያስተናገደችው እንግሊዝ፣ የምግብ አመራረትን አስመልክቶ የሚወጡ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከረኀብ ሊያላቅቁ እንደሚችሉ አስታውቃለች።

ተቺዎች በበኩላቸው፣ በቴክኖሎጂ ላይ የሚደረግ ትኩረት፣ ለምግብ እጥረት ዋና መንሥኤ የኾኑትን፣ እየጨመረ የመጣ የሀብት አለመመጣጠንንና ድህነትን ችላ ይላል፤ ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ሄነሪ ሪጅዌል ከለንደን ያደረሰን ዘገባ ነው፡፡