እሥራኤል ወደ ጋዛ የሚገቡ የእርዳታ መኪኖችን ፍተሻ አጠናከረች

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

እሥራኤል ወደ ጋዛ የሚገቡ የሰብዓዊ እርዳታ ተሽከርካሪዎችን ፍተሻ አጠናከረች

በእሥራኤል-ሐማስ ጦርነት ለተፈናቀሉ ፍልስጥዔማዊያን እርዳታ መድረስ እንዲችል እሥራኤል ይሁንታ ከሰጠችበት ጥቅምት 10 ጀምሮ የተለያዩ ሰብዓዊ አቅርቦቶችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በየቀኑ ወደ ጋዛ እየገቡ ነው።

ተሽከርካሪዎቹ ወደተከበበችው ጋዛ ከመዝለቃታቸው በፊት ግን ጭነታቸው እንዲፈተሽ ወደሚታዘዙበት አቅጣጫ ማምራት ይኖርባቸዋል።

የቪኦኤ ዘጋቢ ናታሻ ማዝጎቫያ ግብፅንና እሥራኤልን ከሚያካልለው ኒትዛና ደንበር የተያያዘውን ዘግባለች።