ደቡብ አፍሪካ እስራኤል የሚገኙ ዲፕሎማቶቿን “ለምክክር” እንደጠራች የሀገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል።
እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት የሲቪሎች ሞት እየጨመረ በመምጣቱ፣ ሀገራቸው ዲፕሎማቶቿን መጥራቷ የተለመደ አሰራር ነው” ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ ናሌዲ ፓንዶር ተናግረዋል።
ደቡብ አፍሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም እንዲሰፍን በመጣር እንዲሁም የፍልስጤማውያንን ጥያቄ፣ ቀድሞ ከነበራት የአፓርትያድ አገዛዝ ጋር በማመሳሰል፣ ስትደግፍ ቆይታለች።
የሕጻናት እና ሲቪሎች ግድያ አሳሳቢ እንደሆነ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል።
የእስራኤልን አቋም በሚተቹት ላይ በፕሪቶሪያ የሚገኙት የእስራኤል አምባሳደር የሚሰጡት አጸያፊ አስተያየትም አሳሳቢ ነው ስትል ደቡብ አፍሪካ ገልጻለች፡፡