ዓመት ያስቆጠረው የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እና ክትያ ኹነቶች በነዋሪዎች አንደበት

Your browser doesn’t support HTML5

ዓመት ያስቆጠረው የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እና ክትያ ኹነቶች በነዋሪዎች አንደበት

ለሁለት ዓመት የዘለቀውና የበርካቶች ሕይወት የጠፋበትን፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት የደረሰበትን የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶርያው ስምምነት ከተፈረመ፣ ዛሬ፣ ጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ.ም. አንድ ዓመት ኾነው፡፡

በዚኽ የአንድ ዓመት የድኅረ ስምምነት ጊዜ፣ ደም አፋሳሹ ጦርነት ከተካሔደባቸው አካባቢዎች ውስጥ፣ በትግራይ እና በአፋር ክልሎች አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል፡፡

በሌላ በኩል የዐማራ ክልል፣ በመከላከያ ኀይል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እና የተለየለት ግጭት ከተቀሰቀሰ አራት ወራትን እያስቆጠረ ነው፡፡

በፌዴራሉ መንግሥት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ-ፕሪቶርያ ስለተፈረመው ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት፣ ስለ ስምምነቱ የሚነሡ ጥያቄዎች፣ በአፈጻጸም ሒደት የክልሉ ነዋሪዎች “ተፈጠሩ” ስለሚሏቸው “ችግሮች”፣ መስፍን አራጌ ከደሴ፣ ከባሕር ዳር እና ከወልዲያ ከተሞች አስተያየቶችን አሰባስቧል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡