በዐማራ ክልል በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት የሰላማዊ ሰዎች ግድያ እንደቀጠለ ኢሰመኮ ገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማራ ክልል በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት የሰላማዊ ሰዎች ግድያ እንደቀጠለ ኢሰመኮ ገለጸ

በዐማራ ክልል፣ የአየር ጥቃትን ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች የሚፈጸም የሰላማዊ ሰዎች ግድያ እንደቀጠለ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ፣ የክልሉን ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክቶ፣ ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ፣ በመንግሥት ኃይሎች ከሕግ ውጭ የሚፈጸሙ ግድያዎች ስለመቀጠላቸው፣ ማሳያዎችን ጠቅሶ አስረድቷል፡፡

የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ሥራ ክፍል ከፍተኛ ዲሬክተር ዶር. ሚዛኔ አባተ፣ አሁን ባለው ኹኔታ፣ ኮሚሽኑ የተሟላ ምርመራ ማድረግ እንደማይችል ገልጸው፣ አጠቃላይ ጉዳቱ በቀጣይ በሚደረግ ምርመራ እንደሚጣራ አመልክተዋል፡፡

ከመንግሥት በኩል ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

ኢሰመኮ በዛሬው መግለጫው፣ በየደረጃው በሚገኙ ሲቪል የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች፣ ግድያዎች እና እገታዎች፣ በታጠቁ ኃይሎች እንደተፈጸሙም ገልጿል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡