የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማጭበርበር ወንጀል በተከሰሱበት እና ግዙፉን የሪል ስቴት ንግዳቸውን ዘለቄታ ፈተና ላይ በጣለውን የክስ ሂደት፡ ጉዳዩን ወደሚያየው የኒው ዮርኩ የማንሃታን ችሎት ዛሬ ተመልሰዋል።
ሆኖም የኒውዮርኳ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሌቲሺያ ጀምስ ቁልፍ ምስክር አድርገው ያቀረቧቸው የዛሬ በባለ ጋራቸው የቀድሞው የሕግ ጠበቃቸው ማይክል ኮኽን በጤና እክል ሳቢያ የምስክርነት ቃላቸውን የሚሰጡበት ወደሚቀጥለው ሳምንት እንዲተላለፍላቸው በመጠየቃቸው በዛሬው ችሎት እንደማይተያዩ ተነግሯል።
ኮኸን ቀድሞ ትዊተር ተብሎ ይጠራ በነበረው በኤክስ ገጽ ላይ ባሰፈሩት አስተያየት፣ ትራምፕን ላለማየት ብዬ ያደረጉት አይደለም ብለዋል። ከኮኽን ይልቅ፣ ትራምፕ በዛሬው የችሎት ውሏቸው የድርጅታቸው ረዳት ተቆጣጣሪ የነበሩት ዶና ኪደር የምስክርነት ቃል ዳግም ኪሚጀምሩበት ቀን ጋር ተገጣጥሟል።
ትራምፕ የሰራሁት ጥፋት የለም ሲሉ ክሱን ማስተባበላቸው ይታወቃል።