ተመድ በደቡብ ሱዳን ለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ረገጣ የተጠያቂነት ጥሪ አቀረበ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ተመድ በደቡብ ሱዳን ለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ረገጣ የተጠያቂነት ጥሪ አቀረበ

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የደቡብ ሱዳን መንግሥት፣ “የተቃዋሚዎችን ድምፅ አፍኗል። የብዙኀን መገናኛን ነጻነት እየገደበና በሲቪል ማኅበራት ሥራም ጣልቃ እየገባ ነው፤” ሲል ከሰሰ።

ኮሚሽኑ አክሎም፣ “እነዚኽ የመብቶች ጥሰት፣ የአገሪቱን ተጠያቂነት እና የዴሞክራሲ ሒደት ያዳክማሉ፤” ሲል አስጠንቅቋል።

የሰብአዊ መብት ረገጣዎቹ እና በዜጎች ሕይወት ጣልቃ የመግባት ድርጊቶች፣ በደቡብ ሱዳን የደኅንነት ድርጅት እንደሚፈጸሙ ያመለከተው የመንግሥታቱ ድርጅት፣ ቀደም ሲል ሁለቱ ሱዳኖች አንድ በነበሩበት ወቅት፣ “የካርቱሙ የደኅንነት ድርጅቶች ይጠቀሙባቸው የነበሩትን የሥቅየት ዘዴዎች የሚያስታውስ አሠራር እየተከተሉ ነው፤” ሲልም ወንጅሏል።

መሐመድ ዬሱፍ ከናይሮቢ ያጠናቀረው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።