የጋቦን ወታደራዊ አመራር ለለውጥ ግፊት የሚያደርጉ ጋቦናውያን እንዲታገሡ ጠየቀ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

የጋቦን ወታደራዊ አመራር ለለውጥ ግፊት የሚያደርጉ ጋቦናውያን እንዲታገሡ ጠየቀ

የጋቦን ጦር ሠራዊት የመንግሥቱን ሥልጣን ከተቆጣጠረና ወደ 60 ዓመት የሚጠጋው የቦንጎ ቤተሰብ አገዛዝ ካበቃ፣ ነገ ቅዳሜ፣ መስከረም 19 ቀን አንድ ወር ይሞላዋል።

ዘጋቢያችን ሞኪ ኤድዊን ኪንዴዝካ ያደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተው ግን፣ ወታደራዊው ሁንታ፣ በነዳጅ አምራቿ የምዕራብ አፍሪካ ሀገር፥ የተሻለ ኑሮ የሚጠይቁ ቅሬታ ያላቸው የሠራተኛ ማኅበራት እና ተማሪዎች የሚያሰሙትን የዕለት ከዕለት ተቃውሞ እያስተናገደ ነው።

የሁንታው አመራር በበኩሉ፣ ለለውጥ ግፊት የሚያደርጉ ጋቦናውያን ትዕግሥት እንዲያደርጉ እንደጠየቀ በዘገባው ገልጿል፡፡ በሞኪ ኢዲዊን ኪንዴዝካ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡