በዐማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት እንደተቋረጠ ነዋሪዎች ገልፁ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት እንደተቋረጠ ነዋሪዎች ገልፁ

በዐማራ ክልል፣ በምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች፣ ከትላንት ማክሰኞ ከቀትር በኋላ ጀምሮ፣ የስልክ አገልግሎት በመቋረጡ፣ የዘመዶቻቸውን ደኅንነት ማወቅ እንዳልቻሉ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው፣ የባሕር ዳር እና የዐዲስ አበባ ከተሞች ነዋሪዎች፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ ከተማ እና በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም፣ በደንበጫ እና በዙሪያው፣ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ የስልክ አገልግሎት እንደማይሠራ አረጋግጠናል፤ ብለዋል፡፡

ሰሞኑን፣ ዳግም በተቀሰቀሱት ግጭቶች፣ በየዕለቱ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ በስልክ ስለ ደኅንነታቸው እንደሚጠያየቁ የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ አሁን ላይ ግንኙነቱ መቋረጡ እንዳስጨነቃቸው ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬ ሕይወት ታምሩን፣ በዋትሳፕ መተግበሪያ መረጃ እንዲሰጡን ጠይቀናቸው፣ ለቦርድ ስብሰባ ውጭ ሀገር እንደሚገኙና ምላሽ የሚሰጡንን ሰዎች እንደሚመድቡ በመልዕክታቸው ገልጸውልናል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።