በመቐለ የቀድሞ ተዋጊዎች የጦር ጉዳተኞች አገልግሎት ማዕከል ተመርቆ ተከፈተ

Your browser doesn’t support HTML5

በመቐለ የቀድሞ ተዋጊዎች የጦር ጉዳተኞች አገልግሎት ማዕከል ተመርቆ ተከፈተ

የትግራይ ክልልን መነሻ አድርጎ ለሁለት ዓመታት በዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለተሳተፉ የትግራይ ታጣቂዎች አካል ጉዳተኞች፣ የሚገለገሉበት ማዕከል በመቐለ ከተማ ተከፈተ።

ግንባታውን በማስተባበር የተሳተፈው የትግራይ ክልል አርበኞች ኮሚሽን፣ ማዕከሉ፣ በ180 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተገነባ አስታውቋል። ማዕከሉ፣ ለአካል ጉዳተኞች የሚያስፈልጉ መሠረታዊ መገልገያዎች የተሟሉለት ነው።

በመቶዎች የሚቆጠሩ የጦር አካል ጉዳተኞች፣ ከአራት ወራት በፊት በመቐለ ከተማ ባካሔዱት የተቃውሞ ሰልፍ፣ “አመራሮች ከእኛ ይልቅ በግል ሕይወታቸው ተጠምደዋል፤ ቀጣይ የጉዳተኞች ሕይወት ተረስቷል፤” በሚል፣ ክብካቤ እየተደረገላቸው እንዳልኾነ ቅሬታ አሰምተው ነበር፡፡ ለጦር ጉዳተኞች ተብሎ የሚሰበሰበውን ሀብት፣ አመራሮች እያባከኑት እንደኾነም አቤቱታ አቅርበው ነበር፡፡

ከዚያ ሰልፍ ተሳታፊዎች አንዷ የነበረችው የጦር ጉዳተኛዋ ጸጋ ኢያሱ፣ የመዝናኛ ማዕከሉ መከፈት፣ ለጉዳተኞች መልካም እንደኾነ ተናግራለች።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።