የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ፣ በመጪው ሳምንት ማክሰኞ ይጀመራል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው፣ እንዳለፈው ዓመት ሁሉ፣ ለሁለተኛ ጊዜ፣ በዩክሬን እየተካሔደ ያለውን ጦርነት ዋናው አጀንዳ ያደርጋል።
በማደግ ላይ ያሉ በርካታ ሀገራት ግን፣ ለእነርሱ አንገብጋቢ የኾኑ ሌሎች ጉዳዮችም፣ በጉባኤው ትኩረት እንዲያገኙ ይሻሉ። ልማት፣ የዋጋ ግሽበት እና የአየር ንብረት ለውጥ ጥቂቶቹ ናቸው።
የቪኦኤ የተመድ ዘጋቢ ማርግሬት ባሺር የላከችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።