ተጠያቂዎች ሳይያዙ እንደማይመለሱ የቅበት ከተማ ግጭት ተፈናቃዮች አስታወቁ

Your browser doesn’t support HTML5

ተጠያቂዎች ሳይያዙ እንደማይመለሱ የቅበት ከተማ ግጭት ተፈናቃዮች አስታወቁ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ቅበት ከተማ፣ ሃይማኖትን በለየ ግጭት ተፈናቅለው በቡታጅራ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተጠለሉ ተፈናቃዮች፣ የድርጊቱ ፈፃሚዎች በሕግ ጥላ ሥር ሳይውሉና የተቃጠሉ ቤቶቻችን ሳይገነቡ ወደቀዬአችን ለመመለስ እንቸገራለን፤” ሲሉ ተናገሩ።

የክልሉ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሙሐመድ ኸሊል፣ ለተፈጠረው ግጭት በሽምግልና እርቅ ለማውረድ ጥረት እየተደረገ እንደኾነ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የስልጤ እና የሐዲያ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ በበኩላቸው፣ በወረዳው በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ፣ ምቹ ጊዜ እና ኹኔታ እየተጠበቀ ጥቃት ተፈጽሟል፤ ሲሉ ተናግረዋል።

በግጭቱ፣ የመንግሥት ሓላፊዎችን ጨምሮ የክርስትናም እና የእስልምና እምነት ተከታዮች እንደተጎዱ የጠቀሱት ሥራ አስኪያጁ፣ አንድን ወገን ብቻ ተጎጂ አድርጎ ማቅረብ፣ “ሓላፊነት የጎደለው ነው፤” ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።