በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች እንዳልተመለሱ ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች እንዳልተመለሱ ገለጹ

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ቅበት ከተማ፣ ካለፈው ሰኞ ምሽት አንሥቶ፣ የሃይማኖት መልክ እንዳለው በተገለጸው ግጭት ተፈናቀለው ወደ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ የሸሹ፣ ከአንድ ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች፣ ወደቀዬአቸው እንዳልተመለሱ ተናገሩ።

አሁንም ጥቃትን ሰግተው የሚሸሹ ምእመናን መኖራቸውን፣ ተፈናቃዮቹ ጠቁመዋል፡፡ በተለያዩ ሰበቦች ይፈጸምብናል ላሉት ጥቃት እና በደል፣ መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጣቸውና የሕግ የበላይነትንም እንዲያስከበር ተማፅነዋል።

ከእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት እና ከስልጢ ወረዳ እስከ ዞን አስተዳደር ያሉ ባለሥልጣናትን ምላሽ እና አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ሙከራ ስልካቸውን ስለማይመልሱ አልተሳካም።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የስልጤ እና የሐዲያ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቀስሲ ንጉሤ ባወቀ፣ መንግሥት ችግሩን እንዲፈታ ከወራት በፊት ቢጠየቁም፣ ችላ በመባሉ ግጭቱ መፈጠሩን አስታውቀዋል፡፡ ይኹንና፣ በስልጤ ባህላዊ “ሴራ” ዳኝነት ሥርዐት፣ የግጭቱን መንሥኤ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ እንደኾነ አመልክተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ።