በመቐለ ከተማ፣ ትላንት ኀሙስ፣ በትግራይ ክልል ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጠርቶ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ፣ በኀይል እንዲበተን መደረጉን ተከትሎ የታሰሩት የአራት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስድስት አመራሮች፣ ዛሬ፣ በቀዳማይ ወያነ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲኾን፣ ችሎቱ በዋስ እንዲለቀቁ ወሰነ፡፡
SEE ALSO: ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመቐለ የጠሩት ሰልፍ በኀይል ተበተነይኹንና፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ ከእስር እንዳልተለቀቁ ታውቋል፡፡
ከስድስቱ አመራሮች ጋራ 150 የሚደርሱ ሰዎች አብረው እንደታሰሩ ቢገለጽም፣ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና ቤተሰቦቻቸውንም ማግኘት እንዳልቻሉ ተገልጿል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ።