የምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ የመንግሥት ሽረት አባዜ አህጉራዊ ሰላምን እንዳያውክ የምሁራን አማራጭ መፍትሔዎች

Your browser doesn’t support HTML5

የምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ የመንግሥት ሽረት አባዜ አህጉራዊ ሰላምን እንዳያውክ የምሁራን አማራጭ መፍትሔዎች

የጋቦኑን መሪ ዓሊ ቦንጎን ከፕሬዚዳንታዊ ሥልጣን ያነሣው ያለፈው ሳምንት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት፣ በሦስት ዓመት ውስጥ በቀጣናው የተካሔደ ስምንተኛው መፈንቅለ መንግሥት ነው።

በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና እስያ ጥናት እና ምርምር ማዕከል ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ፣ የቀጣናው ሀገራት የመልካም አስተዳደር ችግር፣ ሙስና እና ያለአግባብ በሥልጣን ላይ የሚሰነበቱ መሪዎች መበራከት፣ ለመንግሥታዊ ሽረቱ መደጋገም መግፍኤዎች እንደኾኑ ያስረዳሉ፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ መፈንቅለ መንግሥት ያደረጉ ወታደራዊ መኰንኖች፣ የሕዝብ ጥያቄዎችን በማስተጋባት ድጋፍ የመሰብሰብ ስትራቴጅን እየተከተሉ እንደኾኑ፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪው ዶክተር ግዛቸው ዐሥራት ያስገነዝባሉ፡፡

ይኸው የወታደራዊ አመራሮቹ የሕዝብን ቀልብ የመሳቢያ ስትራቴጂ፣ አህጉራዊ እና ቀጣናዊ ተቋማት፣ ሕዝባዊ ተቃውሞን በመስጋት ጣልቃ ገብተው ድርጊቱን ለማስቆም እንዳይችሉ እንዳገዳቸው አመልክተዋል።

(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ)