ለሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጭ ማኅቀፎች ግብዓት ማሰባሰቡ እንደተጠናቀቀ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

ለሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጭ ማኅቀፎች ግብዓት ማሰባሰቡ እንደተጠናቀቀ ተገለጸ

በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጭ ማኅቀፎች ላይ፣ ከዐዲስ አበባ ከተማ በቀር ከኹሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ሕዝብ ግብዓት የማሰባሰብ ሥራው እንደተጠናቀቀ፣ ቡድኑ አስታወቀ፡፡

ከ12 ክልሎች እና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ ከማኅበረሰቡ በርካታ ግብዓት እንደተገኘ የገለጹት የብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ የባለሞያዎች ቡድን አስተባባሪ ዶክተር ታደሰ ካሳ፣ ፖሊሲው በሳምንታት ውስጥ እንደሚዘጋጅ አመልክተዋል፡፡

በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያለው የትጥቅ ግጭት፣ የፖሊሲ ግብዓቱን በማሰባሰብ ሒደት ላይ ጫና እንደፈጠረ የገለጹት የቡድኑ አባል ዶክተር ማርሸት ታደሰ፣ በዚኽም ምክንያት ያልተሸፈኑ ሥፍራዎች መኖራቸውን አልሸሸጉም፡፡

የሽግግር ፍትሕ ሒደቱ፣ ከኹሉን አቀፍ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ጋራ ስላለው ልዩነት እና አንድነትም፣ ባለሞያዎቹ አብራርተዋል፡፡

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ዘገባ ያገኛሉ)