የይቭጊኒ ፕሪጎዥንና ሌሎች የቫግነር ግሩፕ መሪዎች ድንገተኛ ሞት፣ ቡድኑ በአፍሪካ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተጽእኖ ለመገምገም ወቅቱ ገና ቢኾንም፣ ለአጭር ጊዜም ቢኾን ሳያስተጓጎለው እንደማይቀር፣ አንዳንድ ተንታኞች እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
ፕሪጎዥን ከነበረው ጠንካራ የግንኙነት መረብ እና ትውውቅ አንጻር፣ የቡድኑን መሪ የመተካቱ ሒደት ጊዜ መውሰዱ ግድ እንደኾነ ተንታኞቹ ተናግረዋል።
የአሜሪካ ድምጿ የናይሮቢ ቢሮ ሓላፊ ማሪያማ ዲያሎ ያደረሰችንን የዘገባውን ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።