በምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ፣ ተፈጸመ በተባለ ክልል ተሻጋሪ የታጣቂዎች ጥቃት፣ አምስት አዳጊዎች እንደተገደሉ፣ ነዋሪዎች እና የወረዳው ባለሥልጣናት ተናገሩ።
ባለፈው ሳምንት እሑድ፣ በኪረሙ ወረዳ ኖሌ በሚባል ቦታ ተፈጽሟል የተባለውን ጥቃት ያደረሱት፣ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱትና ከዐማራ ክልል እንደመጡ የተገለጹ ታጣቂዎች እንደኾኑ፣ ነዋሪዎቹ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
አኹን ላይ፣ የእኒኹ ክልል ተሻጋሪ ታጣቂዎች ኀይል፣ ከወረዳው ዐቅም በላይ እንደኾኑ፣ የኪረሙ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሓላፊ ተናግረዋል።
በጉዳዩ ላይ፣ ከዐማራ ክልል እየተሻገሩ ጥቃቱን አድርሰዋል ከተባሉት አካላት ምላሽ ለማግኘት፣ ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ለጊዜው አልተሳካም፡፡
ይኹንና፣ የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር የውጭ ድጋፍ ሰጪ ግብረ ኃይል ቃል አቀባይ እንደኾኑ የገለጹና መቀመጫቸውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረጉት አቶ ኡመር ሽፋው፣ የዐማራ ተወላጆች ጥቃት ይደርስባቸዋል እንጂ፣ ጥቃት ያደርሳሉ፤ የሚል እምነት እንደሌላቸው፣ ቀደም ሲል ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረው እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።