ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያ የኢትዮጵያን ገበያ ሊቀላቀል ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያ የኢትዮጵያን ገበያ ሊቀላቀል ነው

በቅርቡ ለባለሀብቶች ክፍት የተደረገውን፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ የሚቀላቀል ሁለተኛ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ለመምረጥ፣ ዓለም አቀፍ ጨረታ እንዳወጣ፣ የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ።

የቴሌኮም ኩባንያዎቹን ለመቆጣጠር፣ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ፣ የቁጥጥር ማኅቀፍ እና የአገልግሎት ጥራት ደረጃ መመሪያ እያዘጋጀ እንደሚገኝ፣ የመሥሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዲሬክተር አቶ ሚሊዮን ኀይለ ሚካኤል፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የአገልግሎት ጥራት መጓደል ሲያጋጥም፣ ደንበኞች ቅሬታቸውን ለባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የሚያቀርቡበት አሠራር እንደተዘረጋም አስታውቀዋል፡፡

የኩባንያዎቹ አገልግሎት፣ ትርፍ በሚያስገኙ አካባቢዎች ብቻ እንዳይታጠር የሚቆጣጠር፣ ጠንካራ ሥርዐት እንደተበጀም፣ ምክትል ዋና ዲሬክተሩ ገልጸዋል።

(ዝርዝር ዘገባውን ከላይ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ)