በዚምባብዌ ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት ቀጥሏል

  • ቪኦኤ ዜና
በዚምባብዌ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ

በዚምባብዌ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ

በዚምባብዌ እየተካሄደ ላለው ምርጫ ድምፅ የመስጠት ሂደት ረቡዕ ጠዋት የተጀመረ ሲሆን፣ ምርጫው ዘግይቶ መጀመሩን በመግለፅ ለቅረበው ቅሬታ፣ የዚምባብዌ ምርጫ ኮሚሽን ምክንያቱ "የአቅርቦት ችግር" መሆኑን ገልጿል።

ሁከት እና ብጥብጥ የሞላበት ምርጫ በማካሄድ የምትታወቀውን ሀገር የሚያስተዳድሩት ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ለሁለተኛ እና ለመጨረሻ የስልጣን ዘመን የሚወዳደሩ ሲሆን ከርሳቸው ጋር 12 ተፎካካሪዎች ለምርጫ ቀርበዋል። ዋናው ፉክክር ግን 'አዞው' በሚል ስያሜ በሚታወቁት የ80 አመቱ ምናንጋግዋ እና በ45 ዓመቱ የተቃዋሚ መሪ ኔልሰን ቻሚሳ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

ዚምባብዌ እ.አ.አ በ1980 ዓ.ም ከነጭ አገዛዝ ነፃ ከወጣች ወዲህ የመሯት ሁለት መሪዎች ብቻ ሲሆኑ፣ እ.አ.አ በ2018 በተካሄደው ምርጫ ምናንጋግዋ ቻሚሳን በጠባብ ውጤት ነበር ያሸነፏቸው።

የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት እስከ ሰኞ ድረስ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። የፓርላማ ምርጫው ውጤት ግን ከሐሙስ ጀምሮ መታወቅ እንደሚጀምር ተገልጿል።