ሮስኮስሞስ የተሰኘው የሩሲያ የህዋ ምርምር ተቋም በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ “መሳሪያው ወዳልታሰበ ምህዋር በመግባት የቆየ ሲሆን በዚህ የተነሳም ከጨረቃ አካል ጋር ሊጋጭ ችላል” ሲል አስታውቋል።
ትላንት ቅዳሜ ተቋሙ ከመንኮራኩሩ ጋር ግንኙነቱ እንደተቋረጠበት አስታውቆ ነበር። ሰው አልባ የሮቦት ማረፊያ መሳሪያው በጨረቃ ደቡባዊ ንፍቀ ክበብ ላይ ነገ ሰኞ ያርፋል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ሲሆን ህንድ በሳምንቱ ማብቂያ ላይ መንኮራኩራን አስከትላ ታሳርፋለች ተብሎ ተጠብቋል።
ሳይንቲስቶች የጨረቃን ደቡባዊ ንፍቀ ክበብ ላይ ውሃ ሊኖር ይችላል በሚል ግምት ለማጥናት እየጣሩ ይገኛሉ። ጨረቃ ላይ ውሃ ከተገኘም ለወደፊቱ ለህዋ ላይ ተጓዥ ተመራማሪዎች ዓየር አሊያም የሮኬት ጋዝ ሊሰራበት ይችላል የሚል ግምት አለ።
ሩሲያ በሶቪየት ህብረት ወቅት በጎርጎሮሳዊያኑ 1976 ለመጨረሻ ጊዜ ጨረቃ ላይ መንኮራኩሯን ያሳረፈችው።