በዐማራ ክልል ያጋጠመው የጸጥታ ችግር፣ በመኸር የእርሻ ሥራ እንቅስቃሴ እና ምርት ላይ ተጽእኖ እንደሚፈጥር፣ የግብርና ምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ገለጹ፡፡
የዐማራ ክልል፣ ከፍተኛ የመኸር ምርት ከሚሰበሰብባቸው ክልሎች አንዱ ነው፡፡ ይኹንና፣ በክልሉ የተፈጠረው ወቅታዊ ኹኔታ፣ ከሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የጸጥታ እና የግብአት እጥረት ችግሮች ጋራ ተዳምሮ፣ የዘንድሮው መኸር ሀገራዊ ምርት እንዲቀንስ ሊያደርግ እንደሚችል፣ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማኅበር፣ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ ዶክተር አቡሌ መሐሪ ይገልጻሉ፡፡
በአንጻሩ፣ የግብርና ምጣኔ ሀብት ባለሞያው ዶክተር ደምስ ጫንያለው፣ የሰላም ዕጦት፣ በእርሻ ሥራው ላይ ጫና እንደሚያሳድር ቢያምኑም፣ በክልሉ ያጋጠመው የጸጥታ ችግር፣ በቀጣይ በሚጠበቀው ሀገራዊ ምርት ላይ፣ የጎላ ተጽእኖ እንደማይኖረው ይናገራሉ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።