በኤፈርት ኩባንያዎች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ

Your browser doesn’t support HTML5

በኤፈርት ኩባንያዎች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ

ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋራ በተያያዘ፣ “ሽብርተኝነትን በገንዘብ ይደግፋሉ” ተብለው፣ እግድ ተጥሎባቸው የነበሩ፣ በትግራይ የመልሶ ማቋቋም ኢንዳውመንት ፈንድ ወይም ኤፈርት ሥር የሚገኙ 21 ኩባንያዎች፣ እግዱ እንዲነሳላቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ፡፡

ከኤፈርት ኩባንያዎች አንዱ የሆነው የሱር ኮንስትራክሽን የህግ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ወርቀ ልዑል ግደይ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለፁት፣ እግዱን ተከትሎ፣ ኩባንያዎቹን በጊዜያዊነት እንዲያስተዳድር ተሹሞ የነበረው አካል ኃላፊነትም እንዲሻር ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡

በኩባንያዎቹ ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ የተነሳው፣ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ፣ ባለንብረቶቹ ለፌደራል አቃቤ ህግ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ዝርዝርን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ