የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ከጥቁር ባህር እህል ስምምነት ከወጣች በኋላ ያሻቀበው ከፍተኛ የእህል ዋጋ ለሩሲያ ኩባንያዎች እና ለአለም ድሃ ሀገራት ጠቃሚ እንደሆነ ተናገሩ ።
የአፍሪካ መሪዎችን ለማማለል ያለሙት ፑቲን፣ ቅዳሜ በሴንት ፒተርስበርግ በነበረው በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ሩሲያ ከእህል ዋጋ መጨመር የምታገኘውን ትርፍ ከአፍሪካ እና ከሌሎች ድሃ ሀገራት ጋር ትካፈላለች። ሩሲያ እንደ ዩክሬን ሁሉ ዋነኛ እህል የምትልክ ሀገር ናት።
በአፍሪካም ሆነ በቻይና የሰላም ተነሳሽነት ላይ የተመሰረተ የሰላም ድርድርን ሩሲያ እንደማትቃወም ተነግሯል።
የፑቲን አስተያት የተሰማው ፣ ወደ ሴንት ፒተርስበርግ ለመሪዎች ጉባኤ የመጡት በርካታ የአፍሪካ መሪዎች ዩክሬን ውስጥ ያለውን ጦርነት እንዲያቆም እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተዘረጋውን የእህል ስምምነት እንዲታደስ በተማጸኑ ማግስት ነው።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ለፑቲን "የቀጠለው ግጭት በእኛም ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደርብን ስለሆነ የሰላም ጥሪ የማቅረብ መብት እንዳለን ይሰማናል" ብለዋል።
ሞስኮ ከየዩክሬን ወደ አፍሪካ የሚላከውን እህል መተካት እንደምትችል ፑቲን ቃል ቢገቡም የዩክሬን እህል ለአፍሪካ አሁንም በእጅጉ አስፈላጊ ነው ።ፑቲን በወራት ውስጥ አስር ሺዎች ቶን እህል ለስድስት ሀገራት በወራት ውስጥ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሀሙስ ዕለት "በጣት የሚቆጠሩ ልገሳዎች" የተሰረዘው የጥቁር ባህር እህል ስምምነት የሚያስከትለውን መጥፎ መዘዝ እንደማያስተካክሉ ተናግረዋል።
በጥቁር ባህር ስምምነት መሰረት ፣ የዓለም ምግብ መርሀ-ግብር ባለፈው አመት 725,000 ሜትሪክ ቶን እህል በመግዛት ወደ አፍጋኒስታን፣ ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና የመን ልኳል።
እ.ኤ.አ. ጁላይ 17 ሩሲያ ከስምምነቱ ወጥታ በዩክሬን ወደቦች እና በጥቁር ባህር እና በዳኑቤ ወንዝ ላይ የሚገኙ የእህል መሰረተ ልማቶችን ላይ ድብደባ ከጀመረች በኋላ የአለም የስንዴ ዋጋ በ9% ጨምሯል።