የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በተፈታኞች ቅሬታ ቀረበበት

Your browser doesn’t support HTML5

የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በተፈታኞች ቅሬታ ቀረበበት

- “ችግር አላየኹበትም” - ሚኒስቴሩ

በቅርቡ የተሰጠው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና፣ ልዩ ልዩ ችግሮች እንደነበሩበት የገለጹ ተማሪዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴር መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠየቁ።

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ተማሪዎች፣ “ፈተናው የተዘጋጀው ከጥናታችን ውጭ ነው፡፡ የተሰጠን ሰዓትም፣ ከፈተናው ክብደት ጋራ አይመጣጠንም፤” ሲሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ይኸው ቅሬታ፣ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለትምህርት ሚኒስቴር ቢቀርብም፣ ሚኒስቴሩ እስከ አሁን ድረስ ምላሽ እንዳልሰጠ ተማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ትምህርት

መምህር እንደኾኑ የገለጹልን አቶ ክብርይስፋው ጌታሁን፣ ፈተናው ችግር እንደነበረበት የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ፤ ብለዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ የተጠየቀው የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ቅሬታ የተነሣበትን የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ትምህርት የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና እንደገመገመው ገልጾ፣ “ችግር አላየኹበትም፤” ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።