በሱዳን እየተካሔደ ባለው ጦርነት፣ በሴቶች ላይ ተፈጽመዋል ስለተባሉት ወሲባዊ ጥቃቶች እና በሌሎችም ጾታ ተኮር መዳፈሮች ጉዳይ ምርመራ እንዲከፈት፣ የአገሪቱ የመብት ተሟጋቾች ጥሪ አቀረቡ፡፡
በዋና ከተማዪቱ ካርቱም እና በምዕራብ ዳርፉር ክፍለ ግዛት፣ የፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኀይሎች አባላት፣ ጾታዊ ጥቃቶች ስለ ማድረሳቸው ተአማኒ መረጃ እንዳላቸው፣ ተሟጋቾቹ ተናግረዋል፡፡
ተመድ በበኩሉ፣ በምዕራብ ዳርፉር ውስጥ፣ ቢያንስ 87 አስከሬኖችን የያዙ የጅምላ መቃብሮች ማግኘቱን ተከትሎ፣ ፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኀይሉ፥ ሲቪሎችን በጅምላ እየጨፈጨፈ ነው፤ ሲል ወንጅሏል፡፡ በጅምላ መቃብሮቹ፣ የሴቶች እና የሕፃናት አስከሬኖች እንደተገኙ፣ ተመድ አስታውቋል፡፡
ማይክል አቲት ከጁባ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።