የአፈር ማዳበሪያ ጥያቄያቸው ያልተመለሰላቸው የዐማራ ክልል አርሶ አደሮች ስጋት አይሏል

Your browser doesn’t support HTML5

የአፈር ማዳበሪያ ጥያቄያቸው ያልተመለሰላቸው የዐማራ ክልል አርሶ አደሮች ስጋት አይሏል

በዐማራ ክልል ባሕር ዳር ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች፣ መሬታቸውን አርሰውና አለስልሰው ለዘር ዝግጁ ቢያደርጉም፣ ማዳበሪያ እስከ አሁን አለማግኘታቸው፣ ወቅቱን እያሳለፈባቸው በመኾኑ በእጅጉ እንዳስጨነቃቸው ገለጹ።

በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ወራሚት በተባለ ቀበሌ ያገኘናቸው አርሶ አደሮች፣ ማዳበሪያ እንዲቀርብላቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል።

መሬቱ ማዳበሪያ እንደለመደ የሚናገሩት አርሶ አደሮቹ፣ ያለአፈር ማዳበሪያ ቢዘሩም፣ በሚቀጥለው ዓመት ምርት እንደማይታሰብ ስጋታቸውን አመልክተዋል።

የአገሪቱ ብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ፣ የጅቡቲ ኤምባሲን ጠቅሶ ትላንት ባወጣው ዘገባ፣ ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ፣ በጅቡቲ ወደብ መድረሱንና በአጭር ጊዜ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ለአርሶ አደሩ እንደሚሠራጭ ገልጿል፡

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።