የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እንደ አዲስ እንዲታይላቸው የጠየቁትን፣ የኢ ጄን ኬሮል የፍትሀ ብሄር ክስ፣ የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛው፣ ዛሬ ረቡዕ ውድቅ አድርገውባቸዋል፡፡
ትረምፕ ቀደም ሲል ወሲባዊ ጥቃት በማድረስ አና በስም ማጥፋት ኢ ጂን ኬሮል በመሰረቱባቸው ክስ ጥፋተኛ ናቸው ሲል ክህዝብ የተውጣጡ ዳኞች ለደራሲዋ የ5ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍሉ ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
በኒው ዮርክ ማንሃተን የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ ሉዊስ ካፕላን በሰጡት ባለ59 ገጽ ውሳኔ ከህዝብ የተውጣጡት ዳኞች (ጁሪው) እ አ አ ግ ንቦት 9 የሰጡት ውሳኔ “ እጅግ የተሳሳተም ፍትህ የተዛባበትም አይደለም” ብለዋል፡፡
ኬሮል ትረምፕን “እ አ አ በ1990ዎቹ አጋማሽ ማንሃተን ውስጥ በሚገኝ የልብስ መደብር የመልበሻ ክፍል ውስጥ አስገድደው ደፍረውኛል፡ ከዚያም ባለፈው 2022 “ትሩዝ ሶሺያል” በሚባለው የማህበራዊ ሚዲያ መድረካቸው የፈጠራ ወሬ ብለው ስሜን አጥፍተዋል ብለው ከሠዋቸዋል፡፡
ትራምፕ በበኩላቸው ከህዝብ የተውጣጡት ዳኞች “ከሳሿን አስገድዶ አልደፈረም የሚል ውሳኔ ሰጥተዋል፡፡ የስም ማጥፋት ክሱም በግምት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ስለዚህ የተወሰነብኝ የ2 ሚሊዮን ዶላር ካሣ “ከሚገባው በላይ ነው” ብለው ተከራክረዋል፡፡
ሮይተርስ ለዚህ ዘገባው የትራምፕ እና የኬሮል ጠበቆችን አስተያየት ለማግኘት እንዳልቻለ ጠቅሷል፡፡