ሚካኤል ሺፈራው፣ በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ፣ በተለይም ደግሞ በቲክቶክ እና ኢንስታግራም ላይ የተለያዩ አጫጭር እና ቀላል የምግብ ማብሰል ቪዲዮዎችን በማጋራት፣ እውቅናን እያተረፈ የመጣ፣ የማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ነው። ሚካኤል፣ ከምግብ ማብሰል በተጨማሪ፣ አብዛኛው ማኅበረሰብ የሚመገብባቸውን የጎዳና ምግብ ቤቶችን ቅኝት በማድረግ ያጋራል።
በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ ላይ ከሚሠራቸው ቪዲዮዎች በመነሣት፣ በአሁን ሰዓት፣ በምግብ እና በመጠጥ ላይ ከሚሠሩ ተቋማት ጋራ፣ በማስታወቂያ እና በሌሎች የመተባበር ዕድል ተፈጥሮልኛል፤ ይላል። በቀጣይም፣ ከሥነ ምግብ ባለሞያዎች ጋራ በመተባበር፣ በማኅበረሰቡ ዘንድ በቀላሉ ከሚገኙ የምግብ ግብአቶች፣ የተመጣጠኑ እና ጣዕም ያላቸው ምግቦችን ለማዘጋጀት እየሠራ እንደኾነ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/