በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ለሰባት ዓመታት በመቋረጡ ለችግር እንደተጋለጡ፣ ነዋሪዎች ገለጹ።
የዞኑ ኮምዩኒኬሽንስ መምሪያ፣ ከግንቦት 2008 ዓ.ም. ጀምሮ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠና በዚኽም ምክንያት፣ ከ300ሺሕ በላይ ነዋሪዎች፣ ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንደተጋለጡ ነዋሪዎቹ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
የጊምቢ ኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ በበኩሉ፣ አገልግሎቱ የተቋረጠው፥ ከጸጥታ ችግር በተያያዘ እንደኾነ ጠቅሶ፣ የተዘረጋው ዐዲስ መስመር፣ ባልታወቁ ኀይሎች በመቆረጡ አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ አለመቻሉን አስታውቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።