በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል የተጀመረው ውይይት እንዲቀጠል የጨፌው አባላት ጠየቁ

የኢትዮጵያ ካርታ

በኦሮሚያ ክልል ለቀጠለው አለመረጋጋት እልባት ለመስጠት፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል ተጀምሮ የተቋረጠው የሰላም ድርድር፣ እንዲቀጥል መደረግ አለበት፤ ሲሉ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባላት ጠየቁ፡፡

በክልሉ ምክር ቤት ዓመታዊ ስብሰባ ላይ የተናገሩት፣ የኦሮምያ ክልል የብልጽግና ቢሮ ሓላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ፣ አምስት ዓመት ያስቆጠረው የሰላም ዕጦት፣ በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ፣ የተጀመረው ውይይት እንዲቀጥል መንግሥት ቁርጠኛ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል የተጀመረው ውይይት እንዲቀጠል የጨፌው አባላት ጠየቁ

በታንዛንያ ዛንዚባር፣ መንግሥትን ወክለው በቅድመ ድርድር ንግግሩ የተሳተፉት የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ሓላፊ ኮሚሽነር ከፍ ያለው ተፈራ በበኩላቸው፣ ውይይቱ እንዳልተቋረጠ ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ሰለሞን ተፈራ፣ ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር በአፋጣኝ ቀጥሎ ችግሩ እልባት ካላገኘ፣ “መዘዙ ብዙ ነው፤” ሲሉ አመልክተዋል፡፡

በቅድመ ድርድር ንግግር የተጀመረው ውይይት ቀጣይነት ቅድመ ኹኔታዎችን እንዳስቀመጠ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።