ገባሬ ሠናዮችን አስተሳሳሪው የትውልደ-ኢትዮጵያውያን ተልዕኮ

Your browser doesn’t support HTML5

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች በቴክሳስ

በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ በአንድ በኩል፥ የሚኖሩበት ሀገር የሚሻውን ታታሪነት፤ በሌላ በኩል፥ ትውልድ ሀገራቸው የምትሻውን ድጋፍ፣ በዚኽም በዚያም እያበረከቱ ይገኛሉ።

“የከበረ ሰብአዊ ተልዕኮ” የተባለው ድርጅት ደግሞ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፥ የተሻለ ሕይወት ለመፍጠር ከሚንቀሳቀሱ ገባሬ ሠናይ ድርጅቶች ጋራ የሚገናኙበትና የሚተባበሩበት ማዕከል ለመኾን አልሞ ሥራ ከጀመረ ሰነባብቷል።

ከወጣት በጎ ፈቃደኞች ጋራ በቅርበት የሚሠራው ይኸው ድርጅት፣ ስለ ዓላማው እና ተግባራቱ ለማስተዋወቅ፣ ከሰሞኑ፣ በዳላስ ቴክሳስ የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ዐውደ ትርኢት(ፌስቲቫል) ላይ ተገኝቷል።

ሀብታሙ ሥዩም፥ ከድርጅቱ መሥራቾች፣ የበጎ አገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እና በጎ ፈቃደኞች ጋራ ያደረገው ቆይታ ቀጠሎ ይቀርባል።