“የእርሻ ግብአት በወቅቱ ባለማቅረቡ ምርትን ይቀንሳል” ባለሞያዎች

Your browser doesn’t support HTML5

“የእርሻ ግብአት በወቅቱ ባለማቅረቡ ምርትን ይቀንሳል” ባለሞያዎች

በተያዘው የመኸር እርሻ ወቅት፣ እየታየ ባለው የግብአት እጥረት የተነሳ፣ በመጪው ዓመት የምርት መቀነስ ሊያጋጥም እንደሚችል፣ ባለሞያዎች አስታወቁ፡፡

የግብርና አማካሪው ዶር. ደምስ ጫንያለው እና የኢኮኖሚ ባለሞያው ዶር. አረጋ ሹመት፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ የእርሻ ግብአት ለአርሶ አደሮች በወቅቱ አለመቅረቡ፣ በመጪው ዓመት፣ የምርት መቀነስ እና የምግብ እህል እጥረት ሊፈጥር እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ የሰብል ምርት እጥረቱ፥ በኢንዱስትሪ ልማት እና በውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይም አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው አመልክተዋል፡፡

መንግሥት፥ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት፣ አርሶ አደሮችን እንዲደግፍና በጀትን ከሌሎች ፕሮጀክቶች ወደ ግብርናው በማዞር ችግሩን እንዲፈታው፣ ባለሞያዎቹ መክረዋል፡፡ የግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ፣ 15 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ በመግዛት፣ ለአርሶ አደሮች እያሠራጨ እንደሚገኝ ገልጾ፣ አሁን ያለውን የግብአት እጥረት ለመፍታትም እየሠራ እንደሚገኝ ይናገራል፡፡

አሁን እየታየ ያለው የግብአት እጥረት፣ የምርት መቀነስን ያስከትላል፤ የሚለው ስጋት ግን፣ ጥናት እንደሚያስፈልገው፣ ከዚኽ ቀደም ለአሜሪካ ድምፅ ቃለ መጠይቅ የሰጡት፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶር. ሶፊያ ካሳ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።