ትውልደ ኢትዮጵያዊ-ጣሊያናዊቷ አርቲስት

Your browser doesn’t support HTML5

ትውልደ ኢትዮጵያዊ-ጣሊያናዊቷ አርቲስት

ዓለም ጃዝ በቅርቡ አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ባህል ማዕከል እና ፈንድቃ የኢትዮጵያ ባህል ማዕከል ውስጥ አዘጋጅቶት በነበረው የሙዚቃ ዝግጅት ትውልደ ኢትዮጵያዊ-ጣሊያናዊቷ አርቲስት ሊሊያና መሌ የጣሊያን ጃዝ ሙዚቃዎችን አቅርባለች። የአሜሪካ፣ የጣሊያን እና የኢትዮ ጃዝ ቅንብሮችን ባጣመረው ሙዚቃዎቿ ጣሊያናዊ እና የኢትዮጵያ ታዳሚዎቿን ያስደመመችው ሊሊያና ግን ዋና ሙያዋ ትወና እንደሆነ ትገልፃለች። እ.አ.አ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ከታዋቂ የጣሊያን ፊልም ተዋንያን ጋር በመሆን በተወነችባቸው እንደ ዲስትረቶ ዲ ፖሊዛ (የፖሊስ ወረዳ)፣ ዶን ማቲዮ (አባ ማቲው) እና አሁን በኔትፍሊክስ የፊልም ማሰራጫ አውታር እየታየ ባለው ማርፎሪ የቴሌቭዥን ተከታታይ ድራማም እውቅናን አትርፋለች።

ስመኝሽ የቆየ ከሊሊያና ጋር ቆይታ አድርጋ ስለሙዚቃ እና ፊልም ህይወቷ፣ እንዲሁም ልትሰራ ስለምታስባቸው የጥበብ ስራዎች አነጋግራታለች።