የስፔን የባህር ዘቦች 70 ፍልሰተኞችን ታደጉ

የስፔን የባህር ዘቦች 70 ፍልሰተኞችን ታደጉ

የስፔን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በአንዲት ጀልባ ላይ ተሳፍረው በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ይጓዙ የነበሩ 70 ፍልሰተኞችን መታደጋቸውን አስታውቀዋል።

ግራን ካናሪያ ከተባለችው የስፔን ደሴት 105 ኪ.ሜ ላይ ጀልባይቱን እንዳገኙ ያስታወቁት የጠረፍ ጠባቂዎች፣ ከፍልሰተኞቹ መሃል ሕጻናትም ይገኙበታል ብለዋል።

ፍልሰተኞቹ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ደሴት ተወስደው በቀይ መስቀል እንክብካቤ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል።

ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ወደ 6 ሺሕ የሚጠጉ ፍልሰተኞች ካናሪ ደሴት መድረሳቸውን የስፔን መንግስት አስታውቋል። ይህም ካለፈው ዓመት ሲነጻጸር 31 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።