“ዩናይትድ ስቴትስ እና ቻይና፣ ግንኙነታቸውን በሓላፊነት የመምራት ግዴታ አለባቸው፤” ሲሉ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ተናገሩ።
ብሊንከን አክለውም፣ አለመግባባቶች ወደ ግጭት እንዳያመሩ፣ “ቀጥተኛ ንግግር ማድረግ የተሻለው መንገድ ነው፤” ብለዋል።
ብሊንከን ይህን የተናገሩት፣ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ለማረጋጋት በታለመውና ለሁለት ቀናት በዘለቀው የቤጂንግ ጉብኝታቸው የመጨረሻው ቀን ላይ፣ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ዢጂንፒንግ ጋራ ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።
ኒኪ ቺንግ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።