ከፍተኛ የትምህርት ቤቶች ክፍያ በተማሪዎች እና በማኅበረሰብ ላይ ያለው ጫና

Your browser doesn’t support HTML5

ከፍተኛ የትምህርት ቤቶች ክፍያ በተማሪዎች እና በማኅበረሰብ ላይ ያለው ጫና

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ መሠረት፣ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት፣ ሕፃናት ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሔዱ መሰናክል ከኾኑባቸው ምክንያቶች አንዱ፣ የትምህርት ቤት ክፍያ መናር ነው፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወላጆችንም፣ ከቤት ኪራይ ቀጥሎ የሚያሳስባቸው፣ የልጆቻቸው የትምህርት ቤት ክፍያ ነው።

በየጊዜው እየጨመረ የቀጠለው የትምህርት ወጪ፣ በትምህርት ሥርዐቱ እና በተማሪዎች ሥነ ልቡና ላይ የሚያሳድረውን ጫና አስመልክቶ፣ ነዋሪነታቸውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረጉትን፣ የማኅበራዊ ጥናት ባለሞያ እና የትምህርት ተቋማት አማካሪ አቶ ግርማ ከበደን አነጋግረናል።