ማላዊ የምግብ እጥረት ገጥሟታል - ዩኒሴፍ

 ፎቶ ፋይል ኤል. ማሲና (ቪኦኤ)

ፎቶ ፋይል ኤል. ማሲና (ቪኦኤ)

የተመድ የሕጻናት በጎ አድራጎት ድርጅት፣ ዩኒሴፍ፣ በማላዊ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከተጋረጠባቸው የምግብ እጥረት ለመታደግ 88 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው አስታወቋል።

574 ሺሕ የሚሆኑ ሕጻናት እና 228 ሺህ የሚሆኑ ነፍሰጡር እና አጥቢ እናቶች የተመጣጠነ ምግብ እጦት አደጋ ገጥሟቸዋል ብሏል ዩኒሴፍ።

ሳይክሎን ፍሬዲ በተባለችው አውሎ ንፋስ ምክንያት 659 ሺሕ የማላዊ ዜጎች መፈናቀላቸውን ያወሳው ዩኒሴፍ፣ ይህም ተጨማሪ ችግር ደቅኗል ብሏል።

በ21 አውራጃዎች የሚኖሩ 3.8 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ዋስትና ችግር ገጥሟቸዋል ተብሏል።