በደቡብ ኦሞ ዞን ግጭት 14 ሰዎች ተገደሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ኦሞ ዞን ግጭት 14 ሰዎች ተገደሉ

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ፣ በቦዲ እና ዲሜ ብሔረሰቦች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት 14 ሰዎች መገደላቸውን፣ የአሜሪካ ድምፅ በስልክ ያነጋገራቸው የሀና ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

አለመግባባቱ የተጀመረው በሁለት ሰዎች ግድያ እንደኾነ የጠቀሰው የዞኑ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ፣ ችግሩ በቦዲ እና ዲማ ብሔረሰቦች መካከል ተስፋፍቶ 11 ሰዎች መገደላቸውንና ስድስት መቁሰላቸውን አረጋግጠዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡