ወደ ትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየው የየብስ የሕዝብ ትራንስፖርት ተጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

ወደ ትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየው የየብስ የሕዝብ ትራንስፖርት ተጀመረ

ከመሀል አገር ወደ ትግራይ ክልል፣ ለሁለት ዓመታት ተቋርጦ የቆየው፣ የየብስ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ከትላንት በስቲያ ተጀመረ፡፡

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 14 ቀን 2015 ዓ.ም.፣ በሰላም ባስ በተጀመረው በዚኹ የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ሌሎችንም የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ለማሳተፍ በመሥራት ላይ እንደኾነ፣ የትግራይ ክልል የትራንስፖርት እና የመገናኛ ቢሮ ገልጿል፡፡

የቢሮው ሓላፊ አቶ ታደለ መንግሥቱ፣ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቱን የተሳለጠ ለማድረግ፣ ከአፋር ክልል እና ከፌዴራሉ መንግሥት ጋራ እንደሚሠሩ አመልክተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።