አልቡርሃን በዒድ መልእክታቸው፥ ወደ ሲቪላዊ አስተዳደር እንሸጋገራለን፤ አሉ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ዩናይትድ ስቴትስ የኤምባሲዋን ሠራተኞቿ ከኻርቱም ለማውጣት ትዘጋጃለች

ከሱዳን ዋና ተፋላሚ ኃይሎች አንዱ - ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይል፣ የዛሬውን የዒድ-አልፈጢር በዓል ምክንያት በማድረግ የተደረሰውን ተኩስ አቁም እንደሚያከብር ያስታወቀ ቢኾንም፣ ዛሬም ውጊያው ቀጥሏል። ተፋላሚዎቹ ወገኖች፣ በዓሉን ምክንያት በማድረግ፣ ለሦስት ቀናት ተኩስ እንዲያቆሙ የቀረበው ተማፅኖ ሰሚ አላገኘም።

ውጊያው እንደቀጠለ ቢኾንም፣ የጦር ኃይሎቹ ዋና አዛዥ ጀነራል አብዱል ፋታሕ አል ቡርሃን፣ ስለ ተኩስ ማቆም ጉዳይ ሳያነሡ፣ አገሪቱን ወደ ሲቪላዊ አስተዳደር እናሸጋግራለን፤ ሲሉ ተናግረዋል።

ውጊያው እንዲቆም ዓለም አቀፍ ጥሪው በቀጠለበት፣ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፥ ለሱዳን ሕዝብ በአስተላለፉት የዒድ በዓል መልዕክት፣ ሁለቱን ወገኖች ለማስማማት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

የአሜሪካ ድምፁ ማይክል አቲት እና ማሪያማ ዲያሎ ያስተላለፈችውንና ሌሎችንም ሪፖርቶች ያጣመረውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች፡፡