በዱባይ የመኖሪያ ህንጻዎች ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ 16 ሰዎች ሲሞቱ 9 ሰዎች ተጎዱ

በዱባይ የመኖሪያ ህንጻዎች ቃጠሎ 2015

በዱባይ፤ በተባበሩት ዐረብ ኤመሬትስ በመኖሪያ ህንጻዎች ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 16 ሰዎች ሲሞቱ ዘጠኝ ሰዎች መጎዳታቸውን ባለስልጣናት አስታወቁ።

ትላንት ቅዳሜ ዕለት በሰማይ ጠቀስ ህንጻዎቿ የምትታወቀው ዱባይ ውስጥ ባለውና የከተማውን ምጣኔ ሃብት ይደግፋሉ የተባሉ የቀን ሰራተኞች በሚኖሩበት ታሪካዊው ዲየራ አካባቢ እሳቱ መነሳቱ ታውቋል። አካባቢው የቀን ሰራተኞች በጋራ የሚኖሩበት እና ተቀጣጣይ በሆኑ ችፑድ፣ ፋይዚቶች እና የመታጠቢያ ቤት ጨርቆች የተሞላ እንደሆነ ተነግሯል።

የዱባይ የሲቪል መከላከያ የመገናኛ ብዙሃን ቢሮ የሟቾቹን ቁጥር ይፋ ያደረገ መረጃ ቢያወጣም ባለስልጣናት ግን የአሺየትድ ፕሬስን ጥያቄዎች ለመመለስ ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ኤፒ ዘግቧል።