መፈናቀል የለያያቸው የተነፋፈቁ ቤተሰቦች በደብረ ብርሃን መጠለያ

Your browser doesn’t support HTML5

መፈናቀል የለያያቸው የተነፋፈቁ ቤተሰቦች በደብረ ብርሃን መጠለያ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከሚኖሩ ተፈናቃዮች መሀከል፣ ከቤተ ሰዎቻቸው አባላት ጋራ የተለያዩ ይገኙበታል።

ከቀዬአቸው ትተዋቸው የመጡት የአራት ልጆቻቸው እናት እና ባለቤታቸው እንደምትናፍቃቸው፣ በኀዘን የሚናገሩት ወላጅ አባት፣ አብረዋቸው ያሉት ሦስት ልጆቻቸውም በእናታቸው ናፍቆት እንደሚያስቸግሯቸው ገልጸዋል።

እርሳቸው ልጆቻቸውን ይዘው ከመኖሪያቸው ሲፈናቀሉ፣ ባለቤታቸው ነፍሰ ጡር እንደነበረችና የተወለደውን ልጅም እንዳላዩት የጠቀሱት እኚኹ ወላጅ አባት አቶ ቤትዬ ደርቤ፣ የተፈጠረው የጸጥታ ውጥንቅጥ ቤተሰባቸውን እንዳፈረሰባቸው ያመለክታሉ።

ከኦሮሚያ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን በሚገኙ ስድስት መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ፣ እስከ 30 ሺሕ የሚደርሱ ተፈናቃዮች እየተረዱ መኾኑን ከከተማ አሰተዳደሩ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

ሰሞኑን በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ ተገኝቶ ተፈናቃዮችን ያነጋገረው ዘጋቢያችን መስፍ አራጌ፣ ለዛሬ የአንድ ቤተሰብ ታሪክ ያካፍለናል።

በዚኽ ዙሪያ የተሰናዳውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የተያያዘውን ፋይል ይጫኑ።