የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዳግም ተመዝግበው ፈቃድ ያወጣሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዘንድ የሚስተዋለው የትምህርት ጥራት ችግር እስከሚስተካከል ድረስ፣ የፌዴራል የትምህርት እና ሥልጠና ባለሥልጣን፣ ለዐዲስ ተቋማት ፈቃድ መስጠት ማቆሙን አስታወቀ። ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በዐዲስ መልኩ እያዘጋጀ የሚገኘው የመመዘኛ መስፈርት ሲጠናቀቅም፣ አሁን በሥራ ላይ ያሉት የግል ኮሌጆች እና ዩኒቨርስቲዎች፣ እንደ ዐዲስ እየተመዘገቡ ፈቃድ እንደሚሰጣቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።