ካማላ ሃሪስ በጋና ለደህንነት እርዳታና አጋርነት ቃል ገቡ

Your browser doesn’t support HTML5

ካማላ ሃሪስ በጋና ለደህንነት እርዳታና አጋርነት ቃል ገቡ

ለአንድ ሳምንት ጉብኝት ወደ አፍሪካ ያቀኑ ቀኑት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በጋና ባደረጉት የመጀመሪያ ቀን ቆይታ የ100 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር እርዳታ ለመስጠት ቃል ገብተዋል። አሜሪካ በአፍሪካ አገሮች ላይ ያላት ፍላጎት ከቻይና ጋር ከመወዳደር ያለፈ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ከምክትል ፕሬዚዳንት ሃሪስ ጋር አብራ የተጓዘችው የአሜሪካ ድምጿ አኒታ ፓውል ከአክራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ደረጀ ደስታ ወደ አማርኛ መልሶታል።