የዳያስፖራ ድርጅቶች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የጻፉት ግልጽ ደብዳቤ

አቶ ዮም ፍሰሃ

በቁጥር ከደርዘን በላይ የሆኑ ዓለም አቀፍ ኢትዮጵያዊ የዳያስፖራ ድርጅቶች፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ የገቡትን ቃል አክብረው ዜጎችን ለመጠበቅ እና ቅሬታዎችን ለመፍታት ቆራጥ የማስተካከያ ርምጃዎች እንዲወስዱ ጠየቁ።

15 ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ድርጅቶቹ ጥያቄያቸውን ያቀረቡት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የመቀጠል ብሔራዊ ህልውናዋ አደጋ ላይ እንደሆነ አሳስበዋል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግልጽ ደብዳቤ የጻፉትን የዳያስፖራ ድርጅቶችን ወክለው ያነጋገርናቸው፣ የአሜሪካ ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ጉዳይ ኮሚቴ የቦርድ አባል እና ጸሐፊ አቶ ዮም ፍሥሃ እንደገለጹት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ወሳኝ መፍትሔዎችን በማስተዋል መውሰድ እና በአፋጣኝ በሥራ ላይ ማዋል ይኖርባዋቸዋል፡፡ ይህን ማድረግ ካልቻሉ ግን፣ ኢትዮጵያ ከዚህ የበለጠ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ልትገባ እንደምትችል አሳስበዋል።

በደብዳቤው ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም ሆነ ከመንግሥት ጉዳዮች ኮምዩኒኬሽንስ ጽ/ቤት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ሆኖም ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽ/ቤቱ በፌስቡክ ገፁ ላይ ለድርጅቶቹ የሰጠው ምላሽ በዘገባው ተካቷል።

/ስለ ደብዳቤው ከአሜሪካ ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ጉዳይ ኮሚቴ የቦርድ አባል እና ጸሐፊ እንዲሁም አቶ ዮም ፍሥሓ ጋራ ተከታዩን ውይይት አድርገናል/

Your browser doesn’t support HTML5

የዳያስጶራ ድርጅቶች ለጠቅላይ ሚንስትሩ የጻፉት ግልጽ ደብዳቤ