የ "ሆቴል ርዋንዳው" ፖል ራሰሳባጌና ከእስር ተፈቱ

ፖል ራሰሳቤጌና ከእስር እንደተፈቱ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት አሰታወቁ ።

ፖል ራሰሳባጌና ከእስር እንደተፈቱ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት አሰታወቁ ። ራሰሳባጌና ከእስር የተፈቱት የዩናይትድ ስቴትስን ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ተከትሎ የርዋንዳ መንግስት የተላለፈባቸውን ቅጣት በማቅለሉ እንደሆነ ባለስልጣናቱ አክለዋል።

ራሰሳባጌና በአውሮፓዊያኑ 1994ቱ የርዋንዳ የዘር ፍጅት ወቅት ፣ ያስተዳድሩት በነበረው ሆቴል ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሸሸገው አትርፈዋል። ይህ መልካም ግብራቸውም "ሆቴል ርዋንዳ " የተሰኘው የሆሊውድ ፊልም ሀሳብ መነሻ ሆኗል ።

የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ራሰስባጌና አርብ እኩለ ሌሊት ገደማ ከእስር ከተፈቱ በኀላ እንዲፈቱ ሰትሰራ በሰነበተችው ካታር አምባሳደር መኖሪያ መወሰዳቸውን፣ ወደ ካታር ከማቅናታቸው በፊት ጥቂት ቀናት በዚያው እንደሚቆዩ ተነግሯል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ አንተኒ ብሊንከን ፣ ራሰስባጌና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ዳግም መገናኘታቸው እፎይታ እንደሆነ ፣ ይሄ ይሳካ ዘንድ የርዋንዳ መንግስት ላደረገው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል ። ብሊንከን ራሰስባጌና ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲመለሱ ለማድረግ ካታር ላደረገችው ድጋፍ አመስግናዋል ።

የ68 ዓመቱ የቀድሞ የሆቴል ባለሟል የአሁኑ የመንግስት ተቃዋሚ የተሳፈሩበት አውሮፕላን ወደ ብሩንዲ ከማቅናት ይልቅ ርዋንዳ ኪጋሊ ካረፈበት ከአውሮፓዊያኑ ነሃሴ 2020 ጀምሮ በእስር ቆይተዋል።


በቀጣይ ዓመት በበርካታ ከሽብርተኝነት ጋር በተሳሳሩ ወንጀሎች ተሳትፎ ተከሰዋል ፣ የፖል ካጋሜን አገዛዝ ከሚቃወም ተቋም ጋር ባላቸው ግንኙነት ምክንያትም ጥፋተኛም ተብለዋል ። ክሱን ሲቃወሙ የሰነበቱት ራሰስ ባጌና 25 ዓመት ተፈርዶባቸው ነበር ።