የበጎ ፈቃድ ሐኪሞችን በማስመጣት የሕፃናትን ሥቃይ ያቃለለው ገባሬ ሠናዩ አስጎብኚ

Your browser doesn’t support HTML5

የበጎ ፈቃድ ሐኪሞችን በማስመጣት የሕፃናትን ሥቃይ ያቃለለው ገባሬ ሠናዩ አስጎብኚ

በተሰማራበት የአስጎብኝነት ሥራ ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋራ በመነጋገር፣ በትውልድ ስፍራው በተለይ በገጠሩ አካባቢ ያሉ በተፈጥሮ የከንፈር እና ላንቃ መሠንጠቅ ችግር ለአጋጠማቸው ሕፃናት መፍትሔ ያመጣውን ወጣት ዛሬ እናስተዋውቃችኋለን፡፡

ወጣቱ፣ ሀብታሙ ጌታቸው ይባላል። ትውልዱም እድገቱም በባሕር ዳር ከተማ ነው፡፡ ሀብታሙ፣ ከ15 ዓመት በፊት በከፈተው ጣይቱ በተሰኘ አስጎብኚ የጉዞ ድርጅት እየሠራ፣ በዚኹ አጋጣሚ ከአገኛቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ውብሸት(ዶ/ር) ጋራ በመነጋገር፣ በአሜሪካን ሀገር የሚገኘው ለም አቀፍ የሕፃናት ቀዶ ሕክምና(Children Surgery International) ሐኪሞች ቡድን ወደ ኢትዮጵያ - ባሕር ዳር እንዲመጡ ይጋብዛል።

ኹኔታዎችን በማመቻቸትም የበጎ ፈቃድኪሞችን ለስምንት ጊዜያት ያህል ወደ ባሕር ዳር ከተማ መጥተው፣ ነፃ የቀዶ ሕክምና እንዲሰጡና በርካታ ሕፃናት ከሥቃያቸው እንዲገላገሉ አድርጓል። ርቀው ከሚገኙ የገጠር አካባቢዎች እየተጓዙ ስንቅም ኾነ መሳፈሪያ ገንዘብ ለጨረሱ ወላጆችም አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል።

ይህን ገባሬ ሠናይ ወጣት ለዛሬ እንግዳችን አድርገነዋል።