“የትግራይን ጸጥታ እና ግዛታዊ አንድነት በማረጋገጥ ላይ አተኩረን እንሠራለን” - አቶ ጌታቸው ረዳ

Your browser doesn’t support HTML5

“የትግራይን ጸጥታ እና ግዛታዊ አንድነት በማረጋገጥ ላይ አተኩረን እንሠራለን” - አቶ ጌታቸው ረዳ

በትግራይ ክልል የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በክልሉ ሰላምንና ጸጥታን በማስፈን እንዲሁም ግዛታዊ አንድነትን በማረጋገጥ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ተናገሩ፡፡

በትናንትናው ዕለት፣ በክልሉ የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እንዲኾኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሾሙት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በዛሬው ዕለት ለብዙኀን መገናኛዎች በሰጡት መግለጫ፣ አስተዳደራቸው ከፌደራሉ መንግሥቱ ጋራ ተቀራርቦ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

“ሒደት፣ የጦርነቱን ምክንያቶች የሚፈታና በዚኽም ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅማችን እንዲሁም የራሳችን ዕድል በራሳችን የመወሰን መብታችን እንዲረጋገጥ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን፤” ብለዋል።

“ምዕራብ ትግራይ፣ ደቡብ ትግራይ፣ የሰሜን ምዕራብ ትግራይ አካል የኾነው ፀለምት ወደ ነበረበት መመለስ እና ጥያቄ ካለ በሕገ መንግሥቱ ብቻ መፈታት እንዳለበት በመግለጫቸው ያሳሰቡት አቶ ጌታቸው፤ “የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ይህን እንዲገነዘቡና የተጀመረውን የሰላም ሒደት ከሚያደናቅፉ ተግባራት እንዲቆጠቡ አደራ ለማለት እፈልጋለሁ፤” ብለዋል።

በጉዳዩ ከአማራ ክልል እና ከፌዴራሉ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ።