የአሜሪካ ም/ፕሬዚዳንት አፍሪካን ሊጎበኙ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በመጪው ሳምንት አፍሪካን ይጎበኛሉ ተብሏል። አፍሪካን የጎበኙ ትልቁ የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣን ያደርጋቸዋል።

ጋና፣ ታንዛንያና ዛምቢያ ለጉብኝቱ ዕቅድ የተያዘላቸው አገሮች መሆናቸው ታውቋል።

ጉብኝቱ በጸጥታና ኢኮኖሚ መስክ አሜሪካ ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው ሲል ቢሯቸው አስታውቋል፡

የመጀመሪያዋ ሴት ም/ፕሬዚዳንት መሆናቸውና የቤተሰባቸው የዘር ግንድ ከአህጉሪቱ ጋር ስለሚያስተሳስራቸው ብቻ ጉብኝቱ ትልቅ ግምት የሚሰጠው እንደሆነ ተንታኞች በመናገር ላይ ናቸው።